ኪነ-ጥበብ

ስውር  ምስጢር   በዲ/ን ቴድሮስ ግርማ
ሰባቱን ሰማያት አቋርጦ ወደኛ ለመጣው እንግዳ
በኃያል ፍቅሩ ሊንደው የጸጋችንን ግድግዳ
ሊያስተናግደው ቆርጦ በረትን ያሰናዳ
ወደምስራቅ
ቢሰበሰቡ ነገስታት ዝናውን ሰምተው
  ለሁለት አመታት ተጉዘው ቢመጡ ከምድር ጽንፍ ተነስተው
እጅ መንሻ ቢሰጡት ሳጥኖቻቸውን ከፍተው
ያለ እኔ የለም ብሎ የጥፋት  አዋጅ ያወጀ
፲፬ ዕልፍ ሕጻናት በጭካኔ ያስፈጀ
ብዙ ድንቅ ሲፈጽም ብዙዎች ሲመጡ ወደሱ
ከለምጻቸው ሲነጹ ሙታን በቃሉ ሲነሱ
ስንኩላን ሲራመዱ ድውያን ሲፈወሱ
ህሙማን ሸክማቸውሲቀል ደካሞች ሲጸኑ በርሱ
ምራቁን እንትፍ ብሎ ለውሶ ከምድር አፈር
አይን ሲሰራ በጭቃ  ቀብቶከደረቅ ግንባር
ይህንን ሁሉ ታሪክ ይህን ሁሉ ተዓምር
ሲፈጸም እያየ የማያምን የሚጠራጠር
እሁድ ከርሱ ጋር ውሎ አርብ ከአይሁድ የሚያብር
………………….ያልብ የኔ ነበር

ያልፈጠረበት ይመስል የሌለው ምግባር ደግነት
ለወሬ ለሐሜት ግን በስፋት የሚከፈት
ከሁለቱ አሳና ከአምስት እንጀራ ግብዣ  አብሮ እንዳልተካፈለ
ከአይሁድ አብልጦ ‘ጮሆ   ይሰቀል ‘ይሰቀል ‘ያለ
ከሰማይና ከምድር ንጉስ ቄሳርን  ያስበለጠ
ከአንተ ከጌታው ይልቅ በርባንን የመረጠ
ውለታ የማይገባው በደሉ እጅግ የከፋ
ከዲዳነት በፈታው በመድኅኑ ላይ የተፋ
ከአይሁድ ሊቃነ ካህናት ከምኩራብ አለቆች ጋር
ተሰብስቦ ያመሸ በሞቱ ጉዳይ ሲመክር
ቅንጣት እንኳን ያለፈረ አብሎ ሲመሰክር
………………….ያ አፍ የኔነበር
ያጎረሰውን ጣት ነካሽ ኃጢአት በደሉ የከፋ
ከደዌ የፈወሰውን የመድኅኑን ፊት የጸፋ
ለንግግር የሚከብድ ጭካኔ ከፍጥረቱ የከፋ
የፈጠሩትን እጆች ከእጸመስቀሉየሰፋ
በገንዘብ የለወጠ ኃያሉን የጌታውን ፍቅር
ወዳጁን ለርካሽ ዋጋ የሸጠ በ፴ብር
……………….ያእጅ የኔ ነበር
አንተ ግን
ስተፋብህ ስመታህ በቸርነትህ ታገስከኝ
የሰውነቴን ሽታ ክርፋቴን ሳትጸየፍ ‘ልጄ” ብለህ አቀፍከኝ
ከአይሁድ ጋር ወግኜ ጎንህን በጦር ብወጋው
ከጎንህ ውሃ  አፍልቀህ  የጠፋ አይኔን ፈወስከው
ወንበዴ ሳለሁግፈኛ እጄን በሰው ደም ነክሬ ምኖር
በአንዲት ቃል ብቻ ናድከው የኃጢአቴን ክምር
እንደምን ያለ ፍቅር ነው እንደምን ያለ ደግነት
በበት የሚያስተኛ ጎትቶ ለጸባዖት
በሰው አፍ የማይገለጽ  ያልተገኘለት ማሰሪያ
ለፀሀይ እጅግ የላቀ የጸና ከአድማስ ድንጊያ
ስለቱ ከሰይፍ    የተባ ይዞታው ከውቅያኖስ የሰፋ
ምንጩ የማይነገር ……….
በሰማይና ምድር ዘላለም ተንሰራፍቶ የሚኖር
በፀዓዳ ብርሃን የተካው ፍፁም ድቅድቁን ጽልመት
በፅኑ ማህተም የታተመ ጠቢባን ያልተረዱት
…………….እፁብ ድንቅ እውነት
የቱንም ያህል ቢራቀቅ እድሜውን ሙሉ ቢመራመር
ሊፈታው አይችልም ደካማው የሰው ፍጡር
እግዚኦ አንተ ፍታው ይህንን ድብቅ ምስጢር

፳፯/፲/፳፻ዓ /ም ተጻፈ

   
   የት ይገኛል?
የእንባዬን አባሽ ምትክ አልባ እናቴን
የአምላኬን ስጦታ ገጸ በረከቴን
በስንጥቅ መነጽር በድንግዝግዝ አይተው የሐሰት ናት ይሉኛል
የአይኔን የጆሮዬን የአንደበቴን እውነት አትመን ይሉኛል
ግና….ልቤ እንዲህ ይለኛል
ከህይወት እስትንፋስ ከአየር ተጣልተው ህይወት የት ይገኛል?

፳፫/፲፩/፳፻ዓ/ም ተጻፈ
 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 



1 comment: