አንቀፀ ተዋህዶ

 
                                              

                                                                       ሰንበት ትምህርት       
ሰንበት ትምህርት ቤት ማለት የጾታ ልዩነት ሳይደረግ መንፈሳዊ ወጣቶችን በዕለተ ሰንበት: በዓበይት በዓላትና አመቺ በሆነ ጊዜ ሁሉ በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን እየተገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት: ሥርዓትና ምግባር የሚያጠኑበት ትምህርት ቤት ነው:: መንፈሳዊ ወጣቶች የሚባሉት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ትምህርተ ሃይማኖት: ሥርዓትና ትውፊት የሚማሩበት ዕድሜያቸው ከ፯- ዓመት የሆነ ወንዶችና ሴቶች ናቸው:: (ቃለ ዓዋዲ ፲፱፻፺፩):: የሰንበቴና የጽዋ ማኅበራት፡ ከቤተ ክርስቲያን ውጭ በመንደርና በሆስፒታል ወዘተ የሚደረጉ ጉባኤያትና የስብከተ ወንጌል መርሐ ግብሮች ሰንበት /ቤት አይባሉም::(ውስጠ ደንብ አንቀጽ ፩፡ ቁጥር )::
                                                //ቤት በዘመነ ብሉይ
የሰንበት /ቤት ከዘመነ ብሉይ ጀምሮ የነበረው ነው፡፡ ለምሳሌ በዘዳግም "እነዚህ ቃሎች በልባችሁና በነፍሳችሁ አኑሩ እነርሱንም ለምልክት በእጃችሁ ላይ እሰሩአቸው በአይኖቻችሁም መካከል እንደክታብ ይሁን ልጆቻችሁንም አስተምሩአቸው በቤትህም ስትቀመጥ በመንገድህም ስትሄድ ስትነሳም አጫውታቸው" የሚል እናነባለን (ዘዳ 1÷6-9)

ከዚህ በላይ እንደተጠቀሰው እስራኤላውያን ልጆቻቸውን ሕገ እግዚአብሔር እንዲያስተምሩአቸው ታዘዋል በትእዛዙም መሰረት ሕፃናቶቻቸውን በቤተ እግዚአብሔርና በቤታቸው ሕገ ኦሪትን እያስተማሩ ያሳድጉቸው እንደነበር ለማወቅ እንችላለን፡፡
                                                   //ቤት በዘመነ ሐዲስ
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ባስተማረበት ዘመንም ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀርበው በመንግስተ ሰማያት ከሁሉ የሚበልጥ ማን ነውባሉት ጊዜ አንድ ሕፃን ጠርቶ በመካከላቸው አቆመ /እውነት እውነት እላችኋለሁ ካልተመለሳችሁ እንደ ሕፃናትም ካልሆናችሁ ወደ መንግስተ ሰማያት ከቶ አትገቡምብሎ ሕፃናትን ለቤቱ ስራ ምሳሌ አድርጎ እንዳቀረባቸው እንረዳለን፡፡ ስለ ትሕትናም ለማስተማር በፈለገ ጊዜ አንድ ሕፃን 
ጠርቶ ሰው ለክብር ቢወድ ከሁሉ በኋላ የሁሉም አገልጋይ ይሁንካለ በኋላ እንደዚህ ካሉ ሕፃናት አንዱበስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔን ይቀበላልበማለት ሕፃናት ለሁሉም ምሳሌ እንደሆኑ ተናግሯል፡፡ / ማቴ 17÷ 2-4  ማር 9÷35-36 ሉቃስ 9÷46-47/
በሌላውም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ሕፃናትን ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲመጡ አይተው ይገስጻቸው ጀመር እርሱ ግን ሕጻናትን ተዋቸው ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ አትከልክቸው መንግሥተ ሰማያት እንደ እነርሱ ላሉት ናትና / በማለት ወደ እግዚአብሔር መቅረብ የሚገባቸው መሆኑን አስገንዝቸዋል /ማቴ 19 14/ በመሆኑም //ቤት በዘመነ ሐዲስ ይበልጥ እንደተስፋፋ  ተረጋግጧል፡፡
ይህንን መሰረት በማድረግ ቤተክርስቲያናችን ሕገ ወንጌልን ለማስፋፋት ከሚያስፈልገô ዋና ዋና ነገሮች አንዱ የሰ//ቤትን ማደራጀት መሆኑን ተገንዝባ //ቤትን በየአጥቢያ ቤተክርስቲያን በስፋትና  በጥልቀት በማደራጀት አድርጋለች፡፡


በአገራችን በኢትዮጵያም በዘመናዊ መልክ እንደ አሁኑ ከሁሉ በፊት እንደ ነበር የታመነ ነው፡፡ ይኽውም በኢትዮጵያ ሊቃውንት ወይም መምህራን በየቤተክርስቲያኑ በየደጀ ሰላሙና በየዛፉ ስር በየመንደሩም ጭምር ሕጻናትን በመሰብሰብ ያስተምሩት የነበረው የሰንበት ትምህርት ቤት መሰረትና መነሻ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡                                                  
በአገራችን በኢትዮጵያም በዘመናዊ መልክ እንደ አሁኑ ከሁሉ በፊት እንደ ነበር የታመነ ነው፡፡ ይኽውም በኢትዮጵያ ሊቃውንት ወይም መምህራን በየቤተክርስቲያኑ በየደጀ ሰላሙና በየዛፉ ስር በየመንደሩም ጭምር ሕጻናትን በመሰብሰብ ያስተምሩት የነበረው የሰንበት ትምህርት ቤት መሰረትና መነሻ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡    

                                     
የሰንበት ትምህርት ቤት ዓላማ
            የሰንበት ትምህርት ቤት ዓላማ በመምሪያው የውስጥ ደንብ ቁጥር  እንደሚከተለው ነው  
 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓት ተጠብቆ ሳይለወጥ ሳይበረዝ ከትውልድ ወደ   ትውልድ እንዲተላለፍ ማድረግ::
  • ማንኛውም የቤተ ክርስቲያኒቱ ተከታይ የሆነ ምእመን የሃይማኖቱን ሥርዓት በውል እንዲያውቅና እንዲረዳ ማድረግ::
  • ወጣቶች የቤተ ክርስቲያንን ሕግና ሥርዓት ተምረው ወላጆቻቸውንና ታላላቆቻቸውን አክባሪ ለሀገርና ለወገንም መልካም ዜጎች እንዲሆኑ ማድረግ::
  • በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ የሚለውን የአምላክ ትዕዛዝ ወጣቶች እንዲፈጽሙ ማስቻል:: (መክ፲፪፡፩)
   የሰንበት ትምህርት ቤት አባልነት
          የሰንበት ትምህርት ቤት አባል:-
  • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓት መከተል
  • ከቅዱስ ሲኖዶስ የሚወጣውን መመሪያ አክብሮ መቀበል
  • ለሕገ ቤተ ክርስቲያን መገዛት
  • በማንኛውም ጊዜና ሥፍራ አርአያና ምሳሌ መሆን
  • የቃለ ዓዋዲውንና የመምሪያውን ውስጠ ደንብ ድንጋጌዎች ማክበርና መፈጸም
  • በሰንበት ትምህርት ቤት የሚሰጠውን ትምህርት መከታተል አለበት::
እነዚህን ከላይ የተዘረዘሩትን ግዴታዎች በማይወጣ የሰንበት ትምህርት ቤት አባል ላይ ከምክር ጀምሮ ከሰንበት ትምህርት ቤቱ እስከ ማሰናበትና ቅጣቶችም ሊወሰኑበት ይችላሉ

          ለሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ትምህርት የሚሰጠው:-
  • ከአስተዳዳሪው ጀምሮ በተመረጡ የቤተ ክርስቲያኑ ካህናት
  • ለሰንበት ትምህርት ቤቱ በተመደቡ መምህራን
  • ከሚመለከተው የቤተ ክህነት /ቤት በሚላኩ መምህራን
  • የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳደር ሲፈቅድ በሥራ አመራር ኮሚቴው ወይም በሰንበት ትምህርት ቤቱ መምህር በተጋበዘ መምህር
  • ከሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች መካከል ሥልጠና ተሰጥቶት ማስተማር የሚችል መሆኑ የተረጋገጠ፡ ሰበካ ጉባኤው የፈቀደለትና የሚሰጠው ትምህርትም በጽሑፍ ተወስኖ የተሰጠው መምህር
              መዝሙርና የመዝሙር መሣሪያ በተመለከተ:-
በሰንበት ትምህርት ቤት የሚዘመረው መዝሙርና የመዝሙር መሣሪያዎች በውስጠ ደንቡ አንቀጽ ፳፮ ላይ ተደንግጓል:: በድንጋጌው መሠረት የሚዘመረው መዝሙር: ዜማውና ምስጢሩ ኦርቶዶክሳዊ መሆኑ በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ በኩል በሊቃውንት የተጠናና በቅዱስ ሲኖዶስ የጸደቀ:: በዚህም መሠረት ከበሮ: ጸናጽል: መቋሚያ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የምንገለገልባቸው ሲሆኑ: በገና: መሰንቆ: መለከት: ዋሽንትና እንዚራ ደግሞ በውጭ አገልግሎት የሚውሉ መሆናቸው ተገልጿል::

              ዝክረ አንቀጸ ተዋህዶ

አንቀፀ ተዋዶ ሰ ትምህርት ቤት 1962 / ለመጀመሪ በደንዮድኃኔዓ / የመጽሐፍቅዱስ ማኅበር በሚል ስያሜ ተመሰረተ በምስረታዉም ወቅት ወ/ሮ  አሰለፈች ገብረ ወልድ ፣ወሮ እጅጋየው  ፣ወ/ሮ ፀሀይ ሀይሌ አቶ መንግስቱ በልሁ አቶ ጌትነት ወንድአፍራሽ፣፣ አቶ ታደሰ ደስታ ፣ወሮ ሐመልማል ፣ወሮ አስናቀች መኮንን፣ወሮ ዘውድነሽ ዋቢ እናየመሳሰሉት የአካባቢው ወጣቶች በመሰባሰብ ቃለወንጌልን ይማማሩ ነበር ከዚህም በተጨማሪ   በተለያዩ ንዑስ ክፍሎችን በመክፈል በተለያዩ የአገልግሎት ዘርፎች  ውስጥ የአጥቢያው  ወጣቶች ያገለግሉ እንደነበር ይታወሳል ።

በምስረታውም ወቅት መዝሙሮን ተቀናጅተው ማቅረብ ባይችሉም ከየአጥቢያው ቤተክርስትያን ሄደው በመመልከት አገልግልት ሊጀምሩ ችለዋል አገልግሎት ሲጀመርም የደንብ  ልብስ በአባላት መዋጮ እንዲሁም በተለያዩ ገቢ ማስገኛዎች እንዲዘጋጅ ተደርጎ የመጀመሪያውን የአገልግሎት የደንብ  ልብስ ተሰርቶአል ይሁን እንጂ  የአገልግሎት የደንብ  ልብሱን  ማስቀጫ ቦታ ባለመኖሩ ወሮ ፀሀይ ሀይሌ ቤት በእናታቸው ፍቃድ በማስቀመጥ  ይጠቀሙ ነበር ።
በደብሩ ሲያገለግሉ የነበሩት አለቃ ይትባረክ ከተቀየሩ በኋላ እንዴት ፈቃድ ሳይኖራቼሁ ታገለግላላችሁ በመጀመሪያ  ቤተክህነት መፍቀድ አለበት ተባሉ  በዚህም ጊዜ ደብዳቤ ጽፈው ከበሮ ይዘው ለወቅቱ  ፓትርያሪክ ከነበሩት ከብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ጋር ሄደው ደብዳቤያቸውን አነበቡ ብጹዕ አባታችንም ‘ ትምህርት ባላኛችሁበት በዚህ ዘመን እዚህ ድረስ መምጣታችሁ ጥሩ ነው ብለው ወዲያውኑ ለደብዳቤያቸው ምላሽ  የሚሆን ደብዳቤ ተሰጣቸው በጣም ተደሰቱ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በነጻነት ማገልገል ጀመሩ በጊቢው የነበረውን የቅዱስ ሚካኤል ሰንበቴ ቤት  እንዲያገለግሉበት ተሰጣቸው ከዚያም የአባላት ቁጥር እየጨመረና እያደገ በመሄዱ ከቤተክርስትያኑ በስተምስራቅ በቤተልሄሙ አቅጣጫ  ያለውን አዳራሽ  ለአገልግሎት  እንዲጠቀሙበት ተሰጣቸው

የአባላቱ ቁጥር እየጨመረ ስለሄደ ተሰጥቶአቸው የነበረው አዳራሽ ሊበቃቸው  አልቻለም ነበር በ 1968 ዓ/ም የቤተክርስትያኑን ደጀሰላም እንዲጠቀሙበት ተሰጣቸው ይሁን እንጂ አባላቱ ለቤተክርስትያኑ የሚሰጡት አገልግሎት በመጨመሩ የተነሳ የቀደሞ አዳራሽ ተሰርቶዋል  በተጨማሪም በማህበራዊ አገልግሎቶችም ላይ ተሳታፊ በመሆን በአካባቢው ከጋና ኤንባሲ እስከ ደብሩ ድረስ ደን የሸፈነውንና ለአካባቢው ነዋሪዎች ችግር የነበረውን መንገድ ጫካውን በመመንጠር እንዲሁም በማስተካከል ለመኪናና ለእግረኛ  ምቹ መንገድ ሰርተዋል ከዚህም በተጨማሪም ጥጥ በመፍተል ጋቢ በማሰራት አቅማቸው ደካማ ለሆኑ የአባላት ቤተሰቦች በስጦታመልክ ያበረክቱ ነበር 

በዚያውዓመት 1968 ዓ/ም  ፖለቲከኞች ወደ አባላቱ ውስጥ ለቅስቀሳ ተቀላቅለው ገቡ ከዚያም አባላትን ቀስ በቀስ ወደ ራሳቸው ዓላማ እንዲሳቡ ለማድረግ እንቅስቃሴ አደረጉ ይህ ጉዳይ የቀበሌውንና የደብሩን አገልጋዮች እንዲጋጩ አደረገ ግጭቱም አባላቱን ለእስር ሰንበት ት/ቤቱን ለመፍረስ ዳረገው ሰንበት ት/ቤቱን ካጋጠሙት ፈተናዎች የመጀመሪያው ሆነ ።

ሰንበትትቤታችን 1968 ለጥቂት ወራት ከተዘጋ በኋላ በድጋሚ በወቅቱ ዲያቆን ከነበሩት በቄሰገበዝ ገብረህይወትኪዳኔበ ወንደማቸው ዲ/ን ደሳለኝ ኪዳኔ እንዲሁም በወቅቱ ዲያቆን በነበሩት በሊቀ ትጉሃን ኪዳነማርያምና…… ከአባቶች አባወልደማርያም  ሊቀ ትጉሃን ፀሀይ መኮንን  አባሣህለ ማርያም መምህሬ ሳሙኤል ከሰፈርም ልጆችአለምነሽ ቦጋለ መሰረት ካሳ ከጅማሰፈር  በቀድሞ አጠራር ከቀበሌ 13እና 14 ደግሞ ፍሬህይወት በቀለ ሙሉ ማሞ ፀሀይ ለማ ዘርፍነሽ  አስቴር ልዑልሰገድ እና ሌሎችም አባላት ሆነው በድጋሚ አንቀጸ ተዋህዶ ተመሰረተ።

አባላቱም  ለአገልግሎት የሚውል  የአገልግሎት የደንብ  ልብስና የመጽሐፍ ቅዱስ አስፈለጋቸው አባላቱም ሶስትም አምስትም ብር በማዋጣት  በራሳቸው ወጪ የአገልግሎት የደንብ  ልብስ አሰፉ መጽሐፍ ቅዱስ ለማግኘት ግን ሰዎችን ማጠያየቅ ጀመሩ በገዳመ ኢየሱስ አካባቢም አቶ መስፍን የሚባሉ በጊዜው የጌድዮናውያን ዓለም አቀፍ ማህበር አባልና ስራ አስኪያጅ የነበሩትን ሰው አገኙ  ለአቶ መስፍንምመጽሐፍ ቅዱስ  እንደሚያስፈልጋቻው በማመልከቻ ፅፈው አስገቡ በዚህ እለት እንመጣለን የሚል ምላሽ በወቅቱ አገኙ በተባለው ቀን 3ካርቶን ሀዲስ ኪዳን 2ካርቶን ትልቁን መጽሐፍ ቅዱስ   ይዘውላቸው መጥተው አስተምረዋቸው ሄዱ በተጨማሪም አባላቱ በብፁዕ አባታችን በአቡነ ባስልዮስ መጽሐፍ ቅዱስ ተሰጣቸው።

በመቀጠልም ሰንበት ት/ቤቱ በዚህን በመሰለ አገልግሎት ከቀጠለ በኋለ በ1985 ዓ/ም  በተለያዩ ደብራት በተነሳው የተሀድሶ ትምህርት በአንዳንድ አባላተ መንፀባረቅ ጀመረ በደብሩ አባቶች በመምህራን ትምህርት እንዲሁም ምክር ባለመቀበል ሰንበት ትምህርት ቤቱን ለማፍረስ ሞከሩ ግን አልተሳካላቸውም በሰንበት ትምህርት ቤቱም ጠንካራ መንፈሳዊ አበላት አነዲሁም አባቶች የሰንበት ት/ቤቱን ጥረት በተሳካ መንገድ  በቀድሞ ሁኔታ እንዲቀጥል አድርገውታል  ሰንበት ት/ቤቱ ስያሜውን ያገኘው በደብሩ ስያሜ ጋር በሚስጥር በማዛመድ ሲሆን አንቀጸ ተዋህዶ የሚለውንም ስያሜ ያገኘው ሰንበት ት/ቤቱ ምስረታ ወቅት በነበሩ አባቶች ነበር ሰንበት ት/ቤቱም በአሁኑ ወቅት በተለያዩ አገልግሎቶች የሚሰጥ ሲሆን

 አባለቱም ከአመት ወደ አመት በመጨመር ላይ ይገኛል  አባለቱ በተለያዩያ የዓለም ክፍላትያሉም ሲሆን በተለያዩ የመንግስት እንዲሁም በግል ስራ ውጤታማ አባላትን ለሀገርና ለህዝቡ አበርክቷል በአሁኑም ሰዓት በተለያዩ የአገልግሎት ንዑሳን ክፍሎች ተከፋፍሎ በአጥቢያው የሚገኙትን ወጣቶችና ህፃናት እያገለገሉ ይገኛሉ የሰንበት ትምህርት ቤቱ ዋና አላማና ግቡ ወጣቶች እንዲሁም ህጻናትን በመንፈሳዊ እውቀት አስተሳሰብ እነዲሁም ክህሎት ማደበርና ለቤተክርስትያን አገልጋይ ካህናት እንዲሁም  በዓለማዊ ትምህርታቸው ድጋፍ በመስጠት ለቤተሰብ ለሀገር ተተኪ አለኝታ ትውልድ መቅረጽና ማፍራት ነው ።

የሰንበት ትምህርት ቤቱም በቃለ አዋዲው በቅዱስ ሲኖዶሱ ህግና ደንብ መሰረት የተለያዩ የአገልግሎት መዋቅሮች ያሉት ሲሆን እነዚህም
የሰንበት ት/ቤቱ ንዑሳን የአገልገሎት ክፍላት 

፩ ትምህርት ክፍል                                                        ፮ ልማት ክፍል

፪ መዝሙር ክፍል                                                         ፯ ተራድኦ ክፍል

፫ ኪነጥበብ ክፍል                                                         ፰ መረጃና ግንኙነት ክፍል

፬ ስነስርዓት ክፍል                                                        ፱ ኦዲዮ ቪዥዋል ክፍል

፭ ህጻናት አደራጅ ክፍል                                                ፲ ገንዘብ ያዥና ኦዲተር

ያሉት ሲሆን ከአነዚህን ክፍላት የሚመሩትምኮሚቴዎች ሲኖሩ ተጠሪነታቸውም  ለስራ አመራር ኮሚቴ ነው
ስራ አመራር ኮሚቴውም  በጠቅላላ ጉባኤ (በአባላቱ )የሚመረጥ ነው ። በአሁኑም ሰዓት በስራ አመራርነት የሚገኙትም
መንፈሳዊ ወጣትይገዙ ብዙአየው ሰብሳቢ
መንፈሳዊት ወጣት ሰላማዊት ፋንቱ ም/ሰብሳቢ
መንፈሳዊ ወጣት ሲሳይ በልዳ ጸሀፊ
ሲሆኑ በንዑሳን ኮሚቴው ውስጥም በተለያዩ አባላትበሀላፊነት   የሚገለገሉ ሲሆን በአሁኑም ሰዓት በአጠቃላይ ከ200አባላት በመያዝ እያገለገሉ ይገኛሉ በትምህርትም ረገድ በተለያዩ ጊዜና ወቅቶች እየሰጠ ይገኛል
ለታዳጊ ህጻናትና ለማዕከላዊ ህጻናት
የትምህርተ ሀይማኖት,መጽሀፍ ቅዱስ ጥናት,የቅድሳን ታሪኮች,ነገረ ማርያም,የአብነት ትምህርቶችና
ለአለማዊ ትምህርታቸውም የማጠናከሪያ ትምህርት እየሰጠ ሲሆን
ለወጣቶች
 ቀዳማይ ኮርስ,ካዕላይ ኮርስ,ሳልሳይ ኮርስ ,እየሰጠ ሲሆን በ2007 ዓም የራብአይ ኮርስ የሚሰጥ ሲሆን
ለአባላቱም በትምህርት በስራ በሀገር ውስጥ እንዲሁም ከሀገር ውጭ ለሚገኙ አባላቱ የርቀት ትምህርት ይሰጣል ከዚህም በተጨማሪ አጫጭር ኮርሶች እንዲሁም ስብከቶች በመደበኛና በኮርስ መልክ እየሰጠ ይገኛል 
ሰንበት ት/ቤቱም በአሁኑ ሰዓት በመጠነ ሰፊ አገልግልት ከቤተክርስትያኑ ጋር በመተባበር የአዳራሽ ግንባታ እያደረገ ይገኛል ከዚህም በተ ጨማሪ የተለያዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶች አባላቱን በማሳተፍ በማገልገል ላይ ይገኛል። 
             የእግዚአብሔርን ቃል የነገሩዋችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ ዕብ 13*7
     ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለ መስቀሉ ክቡር አሜን

                                                      












3 comments:

  1. This comment has been removed by the author.

    ReplyDelete
  2. ጥንካርያቹ ያስደስታል ከናንተ ጥሩ ነገር ተምርያለው ከቻላቹ ኮንታክት ብታደደርጉኝ...

    ReplyDelete